የእድሩ ዓላማ

በአንድ ማኀበረሰብ ውስጥ ለሚኖር ሕዝብ በማኀበራዊ ኑሮ ረገድ የእርስ በርስ መረዳዳትና መደጋገፍ ከሁሉ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ዋናው መሠረታዊ የባሕል ጉዳይ በመሆኑ በአባላት መካከል የኃይማኖት ፣ የጐሣ / የጾታ፣ የኑሮ ደረጃና የመሳሰሉት ልዩነቶች ሳይደረግ እንዲሁም የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ሳይገባ በዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የዕድሩን አባላት ለበጐ ተግባር ማስተባበርና ችግሮቹን እንደየደረጃቸው በወቅቱ በማስወገድ አንድን አባል ከሌላው ሳያበላልጥና አድሎ ሳያደርግ ለሁሉም እኩል አገልግሎት መስጠት ነው፡፡

በአባላቱ ወይም በዕድሩ ደንብ በሚያቅፋቸው የአባላት ቤተሰብና ግለሰቦች ላይ ሀዘን ሲደርስ በደንቡ መሠረት እንደሁኔታው ለመረዳዳት ነው፡፡

ከሞት ባሻገር በቁም መርዳት የሰው ልጅ ኑሮው ለብዙ ያልታሰቡ ችግሮችና አደጋዎች የተጋለጠ ነው፡፡ አደጋዎች የሚመጡበትን ጊዜና መጠናቸውን መተንበይና ማወቅ ከሰው ልጅ አቅምና ቁጥጥር ውጭ ስለሆነ በሞት ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን አስከፊ ችግር ለመቋቋም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ አባል ከመሞቱ በፊት በሕይወት ዘመኑ ለመተጋገዝና ለመረዳዳት ዕድሩ አንድ አባል በጠና ታሞ አልጋ ሲይዝ ለህክምና እርዳታ ማገዣ የሚሆን እርዳታ ማድረግ፡፡